በ2018 በጀት ዓመት ካለፉት አመታት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ አቅደው እየሰሩ መሆኑን የደንበጫ -ፈረስቤት - ሰቀላ እና ቢቡኝ አገናኝ አስፋልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ዳኛው ምንባለ ገልጸዋል። የፕሮጀክት ኃላፊው እንደገለፁት በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ዓመታት በአጠቃላይ ከተሰራው ስራ በላይ ለመፈጸም ታቅዷል።
ፕሮጀክቱ በመልካም አፈጻጸም ላይ የነበረ ቢሆንም ባለፉት ዓመታት በተከሰቱ አለም አቀፋዊ፣ ሀገራዊ እና አካባቢያዊ ሁነቶች ምክንያት ግንባታውን በታሰበው ፍጥነት ለማስቀጠል አስቸጋሪ ሆኖ እንደነበር ያነሱት ፕሮጀክት ኃላፊው በ2018 በጀት ዓመት ከ972,539,760.03 /ዘጠኝ መቶ ሰባ ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሽ ሰባት መቶ ስልሳ ብር/ የሚገመት ስራ በማከናወን በመንገድ እጦት እየተንገላታ የሚገኘውን የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር ለማቃለል ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ ሌሎች የአፈር ድልዳሎ እና የማፋሰሻ ስራዎች እንደተጠበቁ ሆነው ከ20 ኪሎሜትር በላይ አስፋልት ለማንጠፍ ዕቅድ መያዙንም ፕሮጀክት ኃላፊው አስታውቀዋል። ለአስፋልት ስራው ወሳኝ የሆኑት 3 የድንጋይ ወፍጮዎች እና አንድ አስፋልት ፕላንት ለስራ ዝግጁ መሆናቸውን ኃላፊው አስረድተዋል።
ምንም እንኳን ኮርፖሬሽኑ ከጊዜ ጊዜ የማሽነሪ አቅሙን እያሳደገ ቢሆንም ከያዛቸው ፕሮጀክቶች ስፋት አንጻር ሁሉንም በራስ አቅም ለመሸፈን ስለማይቻል ባለፉት ዓመታት የኪራይ ማሽነሪዎችን ለማስገባት አዳጋች እንደነበር ያስታወቁት ኃላፊው በዚህ በጀት ዓመት ይህን ሁኔታ ለመቀየር የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልጸዋል። በተለይም ኮርፖሬሽኑ ከያዛቸው ሁሉም ፕሮጀክቶች ብቻ ሳይሆን ሌሎች አቻ ተቋማት ከሚከፍሉት የተሻለ ዋጋ /Unit Rate/ ለተለያዩ ማሽነሪዎች መተከሉንም ገልጸዋል።
እንደ ፕሮጀክት ኃላፊው ገለፃ ፕሮጀክቱ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ለማስቻል የተለያዩ የስራ አይነቶችን ለንዑስ ተቋራጮች በመስጠት ለማሰራት እና የስራ ዕድል ለመፍጠር አቅጣጫ ተቀምጧል። በዚህም መሰረት አንድ ንዑስ ተቋራጭ 400 ሚሊዮን ብር የሚገመት ስራ ውል ወስዶ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ኃላፊው ሌላ ንዑስ ተቋራጭ ለማስገባት ሂደቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን አብራርተዋል።
በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ የታቀደውን ዕቅድ በአግባቡ መፈጸም እንዲቻል ሁሉም የፕሮጀክቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ የፕሮጀክቱ ኃላፊ አቶ ዳኛው ምንባለ አሳስበዋል።