የኮርፓሬሽኑ ፕላንና ቢዝነስ ዲቨሎፕመት ዳይሬክተር አቶ ተገኘ ወርቁ ግልጽ በሆነ መልኩ ለመድረኩ የሚመጥን አጭርና ገላጭ ሰነድ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል። በውይይት መድረኩ የኮርፓሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር መብት አድማስ፣ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ገበያው መንግስቴን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።
የፕሮጀክት ሰራተኞችም በ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም በተገኘው ከፍተኛ እና ታሪካዊ አፈፃፀም የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው እንደ ኮርፖሬሽን የሁሉም አመራርና ሰራተኛ የድካም ውጤት መሆኑን ገልፀዋል። ኮርፖሬሽኑ በ2018 በጀት ዓመት እንደ ፕሮጀክት እጅግ ፈተና ከነበሩ ወሳኝ ግብዓቶች ውስጥ አስፖልት ፕላንት፣ የድንጋይ ወፍጮ እና የአስፓልት ማሽነሪዎች ማሟላት መቻሉ ፕሮጀክቱን አጠናቆ ለመውጣት የሚያስችል ትልቅ አቅም ፈጥሮለታል ነው ያሉት።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ለአስፋልት ማንጠፍ ሥራው ተቀራራቢ ክብደት የሚሰጣቸውን ሌሎች ግብዓቶችም ቀድሞ ለማቅረብ እየተሄደበት ያለውን ርቀት በልዩ ሁኔታ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። የፕሮጀክቱ ሰራተኞችም ፕሮጀክቱን በተቀመጠለት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለመውጣት የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ያልተገደበ ወቅታዊ ፈጣን ውሳኔ እና የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንዳይለየን በማለት ተናግረዋል።
ኮርፓሬሽኑ በ2018 በጀት ዓመት የፊዚካል እና ፋይናሺያል ዕቅድን ዕውን ለማድረግ የፕሮጀክቱ አመራርና ሰራተኞች በከፍተኛ የሥነ ልቦና ዝግጅት እንደሚገኙ ተናግረዋል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር መብት አድማስ::
በፕሮጀክቱ በኩል የቀረቡ የግብዓት አቅርቦት ስጋቶች እንዳይከሰቱ አልመን እንሰራለን፤ ከዚህም በተጨማሪ ለፕሮጀክቱ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ፈጣን እና ውጤታማ የውሳኔ አሰጣጥን እንከተላለን ብለዋል። በመጨረሻም የፕሮጀክቱ አመራርና ሰራተኞች ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማሰማት ውይይቱን አጠናቀዋል።