ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት ከፍተኛ ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መብት አድማስ ገለፁ።

photo of Mr. Mebit
የኮርፖሬሽኑ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ የተከበሩ አቶ ኃይሌ አበበ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማዕድን ኃብት ልማት ቢሮ እና የኮርፖሬሽናችን ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢን ጨምሮ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የማኔጅመንት አባላት እና ሁሉም የዋና ቢሮ አመራሮች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነዉ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መብት አድማስ ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን ትርፍ በማስመዝገብ ስኬታማ ተግባራትን መፈጸም የቻለበት ወቅት ነበር ሲሉ ገልጸዋል። ኮርፖሬሽኑ ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ በመስራት ከፍተኛ ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉን ነው ዋና ስራ አስፈጻሚው የገለፁት።

በተያያዘም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተቋሙን አሰራር በቴክኖሎጂ በማዘመን ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን ከፍተኛ በጀት በመመደብ የተቀናጀ የኃብት አስተዳደር ስርዓት /Enterprise Resource Planning/ ማስለማት የተቻለ ሲሆን ይህም የተቋሙን ኃብት ከብክነትና ብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ በአግባቡ ለማስተዳደር አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።
workers