ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ብቻ ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ስራ በመስራት 256 ሚሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን የኮርፖሬሽናችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መብት አድማስ የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ ለሚዲያ ተቋማት በሰጡት ይፋዊ መግለጫ ገልጸዋል። እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው ገለጻ በያዝነው በጀት ዓመት በዝግጅት ምዕራፍ እና በተግባር ምዕራፍ የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን ጥሩ አፈጻጸም እየተመዘገበ ነው።
በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 6 ቢሊዮን ብር የሚገመት ስራ ለመስራት ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ከፊዚካል ስራ አኳያ የዕቅዱን 68 በመቶ እንዲሁም ከፋይናንሻል ስራ አንጻር ደግሞ ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ስራ በመስራት 256 ሚሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገብ ችሏል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከመደበኛ የስራ ሰዓት ባለፈ ተጨማሪ ሰዓት የመስራት ልምድን እያዳበረ የሚገኘው ኮርፖሬሽናችን ምሽትን ጨምሮ በሶስት ፈረቃ መስራት መቻሉ ከዚህ በፊት በዓመት ማግኘት ይቻል የነበረውን ትርፍ በ6 ወራት ብቻ ለማሳካት እንዳስቻለ ዋና ስራ አስፈጻሚው በሰጡት ገለጻ አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ከስራ ዕድል ፈጠራ አኳያ ለተለያዩ ማህበራት እና ለጉልበት ሰራተኞች በስድስት ወራት ብቻ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የስራ ዕድል በመፍጠር ማሰራት መቻሉን ዋና ስራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል። በተያያዘም ከዚህ ቀደምም ቢሆን የተለያዩ ማህበራዊ ተቋማትን በነጻ በመገንባት፣ የኢኮኖሚ ቸግር ላለባቸው የጤና መድን ሽፋን በመስጠት፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት በመጠገን እና መሰል ተግባራትን በማከናወን ማህበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ልምድ ያለው ኮርፖሬሽናችን በዚህ ዓመትም በሰሜን ወሎ ዞን አንድ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት በነጻ ገንብቶ ለህብረተሰቡ ለማስረከብ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።